በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ድጋፍ በኢትዮጵያ ሶማሌ ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባላሙያዎች የምርመራ ጋዜጠኝነት ስልጠና አዘጋጀ

ጅግጀጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሰኔ 12/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ድጋፍ የሚደረግለትና በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሞያን ለመደገፍ ታስቦ በተዘጋጀ ውድድር ላይ ተሳታፊዎችን ለማብቃት የተዘጋጀ ስልጠና በዘሬው እለት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ መካሄዱ ተገለፀ። በስልጠናው ላይ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃንን ጨምሮ የክልሉ ሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሞያዎችም ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረገው እና በሃገር አቀፍ ደረጃ የጋዜጠኞችን ሞያ ለመደገፍ ብሎም የክህሎት ውድድርን ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የምርመራ ጋዜጠኝነትን በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ተግባራዊ ለማደረግ የሚያስችል ክህሎት በማሳደግ የጋዜጠኞችን ሞያና አቅም የማበልፀግ አላማ እንዳለውም የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። በዚህ ስልጠና ላይ ጋዜጠኞች የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት USAID እና የአሜሪካን መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከያ ማዕከል CDC በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ስለሚካሄዱት የሥራ እንቅስቃሴ ግንዛቤ በማስጨበጥ በእነዚህ ፕሮጀክቶች ላይ የጋዜጠኝነት ሞያን ተከትለው የምርመራ ዘገባ እንዲሰሩ ታስቦም የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ ላይም የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፈርሃን መሀሙድ፤የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅኔር ኢድሪስ እስማኢል እንድሁም የክልሉ ሚዲያና የኮሙኒኬሽን አመራርና ባላሙያዎችም ተካፈለዋል።በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት   በክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ኢንጅኔር ኢድሪስ እስማኢል አብዲ  "በቅድሚያም ሁላችሁም እዚህ የተገኛችሁትን እያመሰገንኩ ይህ ስልጠና በመዘጋጀቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል ስልጠናው በልማት ጋዜጠኝነት ላይ የልምድ ማጎለበቻ መሆኑን እየገለፅኩ በአቅም ግንባታ ስልጠናው የሚሳተፉ ጋዜጠኞች ከስልጠናው በልማት እና በምርመራ ጋዜጠኝነት ብዙ ልምድ ይቀስማሉ ይህም ለሚዲያ ባለሞያዎች ትልቅ ጠቃሜታን ያበረክታል። ከዚህምበተጨማሪ  በሕገ መንግሥቱ የተቀመጡትን የፕሬስ ነፃነት በመጠቀም የክልሉ ሚዲያ ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ የሠላም፣ የልማትና መልካም አስተዳደር ብሎም የዴሞክራሲ ግንባታ ሥራዎችን ለህዝብ በማድረስ በህዝብ እና መንግሥት መካከል አገናኝ ድልድይ በመሆን የተጣለባቸው ሃላፊነት ይበልጥ እንዲወጡ የሚያስችላቸውም ነው። እንደሚታወቀው የክልላችን መንግሥት የማህበረሠቡን የሚዲያ አማራጮችን በማስፋፋት ከሚኒ ሚዲያ ጀምሮ እስከ ትላልቅ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ማሰራጫዎች ተደራሽነትን እያስፋፋ ይገኛል። እነዚህ ተቋማትም ፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎችን ወደ ሕዝቡ በማድረሱ ረገድ ስኬታማ ሥራዎችን እየሠሩ ይገኛሉ። በመጨረሻም ስልጠናውን ያዘጋጁትን የአሜሪካን ኤምባሲ አካላትን እያመሰገንኩ የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስልጠናውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስባለሁ"  ሲሉ ተናግሯል።

በመጨረሻም ፕሮጀክቱ ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት በመጀመሪያው ክፍል ከየክልሉ ለተውጣጡና በሥራ ላይ ከሚገኙ ጋዜጠኞች ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል ይህም በጤና፣ ትምህርትና ግብርና ብሎም ሠብዓዊ እርዳታን በመሳሰሉት የልማት እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የምርመራ ዘገባን መስራት የሚያስችሉ ክህሎቶች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ይሆናል።  በሁለተኛው ክፍል ተሳታፊ ጋዜጠኞች በክልላቸው ልማት ተኮር ዘገባን በመሥራት በሃገር ዓቀፍ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ላይ እንዲሳተፉና ተጨባጭ የሆኑ ዘገባዎች እንዲያቀርቡ የሚያግዝ መሆኑን የስልጠናው አዘጋጆች ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የ8ኛ ክፍል ሚንስተሪ ፈተና በጥሩ ሁኔታ መጀመሩ ተገለፀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ሰኞ፤ሰኔ 11/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በሚገኙ 11 ዞኖች፣ 6 የከተማ አስተዳደሮችና 93 ወረዳወች የ8ኛ ክፍል ሚንስተሪ ፈተና በጥሩ ሁኔታ መጀመሩን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀረ።

ፈተናውን በክልሉ ከ33 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪወች እንደሚወስዱ በኢ.ሶ.ክ.የትምህርት ቢሮ ገልጿል። በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና በአጠቃላይ በ547 ት/ቤቶች በተሳካ ሁኔታ ተጀምሯል።

በተጨማሪም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም አደም መሀድ ፈተናውን መጀመሩን አስመልክተው በጅግጅጋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመዘዋወር የፈተናውን ሂደት ጎበኝቷል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሒም አደን "ዛሬ በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በክልላችን በሁሉም አካባቢዎች በተሳካ ሁኔታ የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጀምሯል። በክልሉ በሚገኙ 11 ዞኖች፣ 6 የከተማ አስተዳደሮችና 93ወረዳዎች በሚገኙ 547 ት/ቤቶች ሚንስተሪ ብሔራዊ  ፈተናው ለ33,713 ተማሪዎች ይሰጣል፤በሠላምና በጥሩ ሁኔታ ይጠናቀቃል ብለንም እንጠብቃለን። በዚህም ለ3 ቀናት በሚቆየው ፈተና ላይ መላው የትምህርት አካላት ተማሪዎች፣ መምህራን እና ወላጆች እንዲሁም የክልል፣ የዞን፤የወረዳ አመራሮችና ባለሞያዎች ልክ እንደ 10ኛና 12ኛ ክፍል ፈተናዎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሁንም  የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲትወጡ እየጠየቅሁ ተማሪዎችም ፈተናውን በአግባቡ ተፈትነው እንዲያጠናቅቁ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ" ሲሉ ገልፀዋል።  

ከዚህ በተጨማሪም 2133 ፈታኞች፣ ተቆጣጣሪዎችና የፈተና ማዕከል አዛዦች በፈተናው ላይ እንደምሳተፉም ቢሮ ኃላፊው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳትእና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም 132 የቴክኖሎጂ ምርምሮች ማዘጋጀቱን አስታወቀ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)አርብ፤ሰኔ 01/2010 .. የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳትና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም በ1994ዓ.ም ከተመሰረተ ጀምሮ የክልሉ አርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር ኑሮ የሚሻሽል በእንሰሳት፤በሰብል ሀብት ልማት ፣ በግብሪና መካናይዜሽንሽ እንዲሁም ሌሎች ግብሪና የሚያቶክሩ  132 የቴክኖሎጂ ምርምሮች  መከናወኑን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ 85 በመቶ የሚሆኑ የክልሉ አርብቶ አደርና ከፍል አርሶ አደር የምግብ ዋስትናና ኢኮኖሚ  ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያከናወናቸው የምርምርና ከህብረተሰብ ጋር  የማላመድ ስራዎችን ለማጠናከር  የተለያዩ ፕሮጄክቶችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ስሆን ከእስዊዘርላንድ መንግስት ጋር በመተባበርም የዲጂታል የዕፅዋት ናሙና አያያዝና ዝናብ አጠር አከባቢ የሚበቅሉ  ፅዋት ለማላመድና ዚሪያዎችን ለማስፋፋት የሚያስችል ፕሮጄክቶች እያከናወነ ይገኛል፡፡

በክልሉ የሚገኙ በርካታ የዕፅዋት ስብስብ ናሙና በዲጂታል በሆነ መንገድ በመሰብሰብ እና ለማቆየት እንዲሁም በሀገራችን በክልሉ ብቻ የሚገኙና በማጥፋት አደጋ ላይ ያሉ እፅዋቶችዝሪያዎች ለማስፋፋት ተቋሙ የሚያከናወነው  የፖሮጀክት አተገባበር ከትላንትናው ዕለት በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሚስተር ደንኤል የሚመራ ልዑኳን ቡድን በተቋሙ ስራዎች ጎበኝቷል፡፡ልዑካን ቡድኑ የክልሉ መንግስት የእንሰሳት እርባታና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም ሀላፊዎች፣ ተመራማሪዎችና ባላዉዎች በተገኙበት መድረክ በጅጅጋ ከተማ ተገኝተው በፖሮጀክቱ እየተካናወኑ ያለው የዲጂታል የእፅዋት አያያዝን፣የዉብተክል የማላመድና ስርቶ ማሳያ እንዲሁም በተቋሙ ሰርቶ ማሳያ መዓከል እየተከናወኑ የሚገኙ የሰብል ምርምር፣ ማላመድና ቴክኖለጂ ሽግግር ስረዎችን ተዛዋዊሮ የጎብኙ ስሆን በተቀሙ ባላሙዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ በጉብኝቱ የተገኙት በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት የእንሰሳት እርባታና ከፊል እርሻ ምርምር ተቋም ም/ዳይሬክተር አቶ አብዱረህማን መሀመድ እንዳሉን የልዕኳን ቡዲኑ ዋና አላማ በምርምር ላይ የሚገኙ ፕፖሮጀክቶችን ተግባራዊነት ለመመልከት እንደሆነ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም  ም/ዳይሬክተሩ “ዛሬ የመጠው የስዊዘርላንድ አምበሳደርና ከጀአይዜድ የመጣ ዴሊገሽ ናቸው፡፡ የጉብንቱ ዋና አላማ የእኛና ጀኣይዜድ ው የትብብር ስራ እንዲሁም ከጂአይዜድ የወሰድነው ሁለት ፖሮጀክቶች ስላሉ ለመከታተልና ለማየት ነው፡፡እነዚህ  ሁለቱ ፖሮጀክቶች አንዱን ሀርፓሪያን ዲጂታላይዜሽን የሚባል ሲሆን ይህ ሀርፓሪያን ከ20 አመት በፊት በክልላችን የተሰበሰበ ዝርያ ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመቀየር ነው በዚህም  ፖሮጀክቱ በጣም ውጤታማ መሆኑን አረጋግጧል። ሀለተኛ ደግሞ ወተር ፖክስ የሚባልና በድርቅና ዉሃ መቆራረጥ በሚኖርበት ወቅት የተለያዩ አትክልት ለመተክል የዝናብ ውሃ ለማጠራቀምና ዉሃን እንዲያዝ የሚንጠቀምበት ነው” ሲሉ ተናግሯል፡፡

በሌላ በኩልም የተቋሙ ተመራማሪዎች በበኩላቸው በፖሮጀክቱ እያተከናወኑ የሚገኙ የዲጂታል  ምርምርና የእፅዋት ናሙና አያያዝ ስራዎች በክልሉ የዝናብ አጠር አከባቢዎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና በዘርፉ ለሚከናወኑት የሚርምር ስራዎች የጎላ ጠቀሜታ እነደሚያበረከቱ አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ብቻ የሚገኝና በዓለም ላይ ተወዳጅ የሆነና ይእብ የተባለ እፅዋት ዝሪያ ከአሁን በፊት በአምስት ዞኖች ላይ እንደነበረና በአሁኑ ወቅት ግን  በዶሎ ዞን ስር የሚገኙ አንዳንድ ቀበሌዎች ብቻ እንደሚገኝ እንድሁም የአከባቢው ህብረሰብ ለምግብ ፣ለቤት መስሪያና ለእንሰሳት ምግብነት ስለሚጠቀሙ በስዊዘርላንድና በጂኣይዜድ ድጋፍ የሚሰራ የምርምርና ዲጂታላይዜሽን ፖሮጀክቶች የይእብ እፅዋት ዝሪያዎች ከአደጋ እንደዳነና አሁንም በስጋት እንደሚገኝም ተመራማሪዎቹ አስረድተዋል።

 

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተከፈተ

ጅግጅጋ(Cakaaranews)ማክሰኞ፤ሰኔ 05/2010ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግሥት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች 8ኛ ቅርንጫፉን መክፈቱ ተገለፀ። በምርቃት ስነ-ሥርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር በክብር እንግድነት በተገኙበት እንዲሁም የመንግሥት ከፍተኛ አመራር አካላት፣ሃገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው በተገኙበት የቅርንጫፉን መከፈት አብስሯል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መመሪያ በጅግጅጋ ከተማ መከፈቱ በክልሉ ለሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር ለክልሉ ተወላጅ ዲያስፖራዎች የትውልድ ካርድ መስጠትና ማደስ ብሎም ለውጭ ሃገር ዜጎች የኦንላይን ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ ለመስጠትና ለማራዘም ወደ መዲናችን አዲስ አበባ ሳያመሩ በዚሁ በክልሉ ቅርንጫፍ ማግኘት እንደሚችሉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉደዮችመምሪያ  ዋና ዳይሬክተር አቶ ገ/ዮሐንስ በመግለፅ በእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑትን የክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ ጋብዘዋል።

"ለኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ይህ ዕለት ትልቅ ታሪካዊ ቀን ነው። የኢትዮጵያን መብት የሆነውን ይህን ፓስፖርት ለማግኘት እጅግ በጣም ረጅምና አድካሚ ጉዞ ካደረጉ ወይንም ከብዙ ችግር በኋላ ነበር ሲያገኙ የነበረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብም ልክ እንደ ማንኛውም የሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች ወይም ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ፓስፖርት በመታወቂያው ማግኘት መብትና ግዴታው ነው ሆኖም ግን ለምሳሌ በኢ.ሶ.ክ ከፌርፌር ጅግጅጋ 1500 ኪ.ሜ ነው ከዚህ በተጨማሪም ከፌርፌር እስከ አዲስ አበባ አድካሚ ጉዞ በማድረግ ነበር ፓስፖርት ለማውጣት ይሄዱ የነበረው። በዛ ውስጥ ብዙ ችግሮች ነበሩ ለምሳሌ ሃጂና ኡምራ ለማግኘት አንድ አርብቶ አደር ያውም ጫካ የሚኖር የሐይማኖት ግዴታውን ለመወጣት ሲል የግድ ወደ ሃጅ መሄድ አለበት ፕሮሰሱን በሚጀምርበት ጊዜ ከቀበሌ መታወቂያ ሲያገኝ አንድ አካባቢ ብቻ አዲስ አበባ ሄዶ ነበረ ፓስፖርት ሲያገኝ የነበረው። እንግዲህ እንደሚታወቀው ይህ አርብቶ አደር ወረዳንና ከተማን አይቶ የማያውቅ ሲሆን ከብዙ ውጣ ውረዶች በኋላ አዲስ አበባ ድረስ በመመላለስ ነበረ ፓስፖርት ለማግኘት የሚደርሱት ሌሎች በርካታ ችግሮችም እንደነበሩ ይታወቃል።"

ክቡር ፕሬዝዳንቱ አያይዘውም "በተለይ ቢሮው ባለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ መሻሻልና ጥሩ ሥራዎች ተሰርተውበት ነበር ምክንያቱም ቀደም ባለው ጊዜ ረጅም ጉዞ ተጉዞ ማግኘትም ጥሩ ነበረ ማለት ይቻላል ከዚህ በፊት ፓስፖርት ፈላጊዎች ተጉዘው ሄደው ላያገኙ የሚችሉባቸውም ጊዜያትም ነበሩ።ነገር ግን በቢሮው ከፍተኛ መሻሻል ስለተደረገ ይሄው ዛሬ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ በጅግጅጋ ከተማ ፓስፖርት የማግኘት መብቱ ስለተረጋገጠ በመጀመሪያ ምሥጋናችንን ለአላህ እናቀርባለን በመቀጠልም ገደብ የሌለው ምሥጋናዬን ለፌዴራል መንግሥትና ለቢሮው አቀርባለሁ። የክልሉን መታወቂያ በዘመናዊ መንገድ የተሠራና በምንም አይነት መልኩ አመሳስሎ (ፎርጅድ) ሊሠራ የማይችል ሲሆን ይሄንን ከቢሮው ጋር ተስማምተን ያደረግነው ሲሆን በተጨማሪም ለሌሎች ክልሎችም ምሳሌ ሊሆን የሚችል አሠራር ነው ክልሉ የዘረጋው” በማለት አብራርተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉደዮች  መምሪያ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገ/ዮሐንስ በበኩላቸው "የጅግጅጋ ኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለኢትዮጵያዊያን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪም በተለያዩ የውጪ ሃገራት ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ለሆኑት የኢትዮጵያ ሶማሌ ልጆች የትውልድ ካርድ የማደስ እና የመስጠት ለውጪ ዜጎች ደግሞ የኦንላይን ቪዛና የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘትና ለማራዘም አዲስ አበባ ሳይሄዱ እዚሁ ሊየዘገኙ የሚችሉበት ሁኔታ ተመቻችቷል።

 በተመሳሳይ የሃገራችንንና የክልሉን ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ገበያን ለማነቃቃት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ከየትኛውም የዓለም ክፍል ለሚመጡ ተጓዦች ሁሉም ቪዛዎች በኤሌክትሮኒክስ ወይም ኦንላይን ቪዛ መስጠት ተጀምሯል ዋና ዳይሬክተሩ ሲሉ ገልፀዋል።በመጨረሻም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎችም የናሙና ፓስፖርት ከፕሬዝዳንቱ እጅ በመቀበል በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል።

የኢ.ሶ.ክ.መ. የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በመንገድ በማስተሳሰር የማህበረሠቡን ልማት ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ተገለጸ

ቀብሪበየህ(cakaaranews)እሮብ:ግንቦት 29/2010ዓ.ም.በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ከቀብሪበያህ ከተማ አስተዳደር እስከ ሀርቲሼክ እየተሠራ ያለው የኮንክሪት አስፋልት መንገድ በተያዘለት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። የክልሉን ዞኖችና ወረዳዎችን በመንገድ መስረተ ልማት ለማስተሳሰር ከሚደረገው የልማት ሥራዎች አንዱ የሆነው ከቀብሪበያህ እስከ ሀርቲሼክ ድረስ ያለውን የ23 ኪ.ሜ ርቀት በኮንክሪት አስፋልት መንገድ ለመሸፈን የተጀመረው ሥራ በታቀደለት ጊዜ እንደሚጠናቀቅ የተናገሩት የቀብሪበያህ ሀርቲሼክ መንገድ ፕሮጀክት ኮንስትራክሽን መሃንዲስ አቶ ሳምሶን ገ/አብ ናቸው።

በዚህም አቶ ሳምሶን ገ/አብ "ሁለት ነገሮችን ነው የሠራ ነው ከጠረጋው ሥራ ጎን ለጎን የካምፕ ኮንስትራክሽንም ሥራ ነበረ በዛም ላይ የሁለቱም ጠረጋ ሥራም ሌላው ነው። ሊፈጅብን የሚችለውም ጊዜ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንጨርሳለን ብለን እናምናለን" ሲሉ ገልጿል።

በጨማሪም የመንገዱ መሠራት በአካባቢው የሚገኘውን ማህበረሠብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳደግላቸው የሚታመን ሲሆን የመንገድ ፕሮጀክቱ መጀመርም የሥራ እድል መፍጠር እንደቻለም ኃላፈው ተነግሯል። በግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ሥራው የተጀመረው የቀብሪበያህ ሀርቲሼክ የኮንክሪት አስፋልት መንገድ ሥራው በተጀመረ በአጭር ጊዜያት ውስጥ የ5 ኪ.ሜ የጠረጋ ሥራና የመንገድ ካርታ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀም የኮንስትራክሽን መሃንዲሱ አብራርቷል።

"አሁን የደረስንበት ደረጃ  5 ኪሎሜትርን የቤንች መሙላት ሥራና የአፈር ጠረጋ ሥራ ጨርሰን  በዲዛይኑ መሠረት የሙሌት ሴክሽን ነው የመጀመሪያ ደረጃ ሙሌት በ15 ኪ.ሜ ውስጥ እየሠራን ሲሆን በቀጣይም የ5 ኪ.ሜ ጠረጋ ሥራዎችን እንሠራለን።" ሲሉ አቶ ሳምሶን ተናግሯል።

በርካታ ሥራዎች እንደሠሩ የተናገሩት የፕሮጀክት ኮንስትራክሽን መሃንዲሱ የ23 ኪሎሜትሩ የጥርጊያ መንገድ ከተጠናቀቀ በኋላ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ እንደሚጀመርም አስረድቷ። የቀብሪበየህ ሀርቲሼክ የመንገድ ፕሮጀክት አንድ የኮንክሪት አስፋልት  መንገድ ሲሆን የፕሮጀክቱን ኮንትራት የወሰደውን  የኢ.ሶ.ክ. ገዢና ልዩ ኮንስተራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከመሆኑ ባሻገር የክልሉ ዲዛይንና ቁጥጥር ኢንተርፕራይዝ በፕሮጀክቱ ኮንስተራክሽን ስራዎች ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግም ተገልጿል።

Amharic News 08_09_10


Amharic News 07_09_10


Amharic News 05_09_10Amharic News 04_09_10Amharic News 26_08_10


Amharic News 25_08_10


Amharic News 24_08_10Amharic News 23_08_10Amharic News 22_08_10


Amharic News 21_08_10Amharic News 20_08_10


Amharic News 19_08_10Amharic News 18_08_10


Amharic News 17_08_10